Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ያዘው

Yazew

4:26 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ጉዳዬን ይዤ ስንበረከክ

ብዬ (እንደ ፈቃድህ)*2

ገና ጉልበቴ ደጅ ሳይጠና

የልቤ ሀሳብ በፊትህ ይቅና

ለምን መልሴን ናፈቅሁ? ለምን መቀበል?

ለምን የሙጥኝ አልሁ? ለምን መታገል?

መርምር ፍላጎቴን የውስጤን መሻት፣

ታውቀዋለህና የልቤን እውነት

የነፍሴ ንግግር የሚገባህ አንተ፣

ስንት ጸሎቴን መለስህ? እርማትን ሰጥተህ፤

እኔ እንኳን ያልገባኝ የውስጥ መሻቴ

ላንተ ጠርቶ ይታያል ግልጽ ነው አባቴ

ዐሥር ነበሩ አብዝተው የጮኹ፣

ፈውስ ፍለጋ የተማጠኑ፣

ምሕረት አግንነህ ብትለመናቸው፣

መልሳቸው ዘጠኙን ካንተ አራቃቸው

ከማይመልሰኝ ከእግርህ ሥር

ደጅ ከሚያስቀር ከሚያባዝን

የቱም መሻቴን ሳትሰጠኝ ያዘው

ከመልሴ ይልቅ ‘ምሻው አንተን ነው

በጎ መልካም ፈቃድህ፣ ይሁን በኔ ‘ሚያከብርህ

ይህን ብቻ ‘ፈልጋለሁ ይሁን ያልከውን አሜን እላለሁ

መና አብልተህ ሥጋ ብለው የጮኹት

ጽኑ ልቅሶአቸው ውስጥ እጅህን ነው የናቁት

ስለ ንዝነዛቸው መሻታቸውን ሞላህ

ተቆጥተሃቸው አምጣ ያሉህን ሰጠህ

ገና ሳይወርድ ከጉሮሯቸው

ስንቶች አለቁ በገዛ አምሮታቸው!

ፈቃድህ ካልሆነው ከሚያጠፋኝ መሻት

ልቤ አያዘንብል ነፍሴ አትጎራበት

ስንት ጸሎት አለ ጸሎት ‘ሚያስፈልገው!

ስንት መሻት አለ ልጓምን የሚያሻው

ያዘው ያዘው ‘ማያከብርህን ምላሼን ያዘው

መሻቴን ሞልተህ ከምትሄድብኝ፤

ሁሉም ይቅርብኝ ያዘው

ያዘው ያዘው ከሕይወት ከምጎ’ል

ካንተ ከምለይ ምላሼን ያዘው፤

በጄ አይግባ ካንተ ልስማማ፤

ሁሉም ይቅርብኝ ያዘው

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ