Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ርህራሄህ

Rihraheh

5:00 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ሙግቴን የረታህ ያሸነፍህልኝ

በበደል መንገድ ላይ፣ በኀጢአት ሳልገኝ፣

መንገዴም የቀና፣ አረማመዴም ልክ፣

ሆኖ አይደል በፊት እህ ፣ በፍርድ ወንበሬ የቆምህ

ገና ሳለሁ በኀጢአት በጨለማ መዳፍ፣

ሕይወት ሰጥተህ ፍርዴን ረታህ፤ ገልጠህ አዲስ

ምዕራፍ

ርኅራኄህ ወደኔ አመጣህ (*2)

ይህ ቅን ልብህ እኔን ማለፍ ቢያቅተው፣

ያለምክንያት ምሕረትን አገኘሁ፤

ይህ ቅን ልብህ እኔን ማለፍ ቢያቅተው፣

ኀጢአተኛዋ ምሕረትን አገኘሁ

በኀይል ቢሆን ከደካሞች ተራ፣

በጻድቃን ማኅበር በኀጢአተኞች ጎራ፣

የምሰለፍ እኔን ለሕይወት ልታስብ፣

ከርኅራኄህ ውጪ እህ ምንስ ሊገኝ ሰበብ?

ርኅራኄህ ወደኔ አመጣህ (*2)

ይህ ቅን ልብህ እኔን ማለፍ ቢያቅተው፣

ያለምክንያት ምሕረትን አገኘሁ፤

ይህ ቅን ልብህ እኔን ማለፍ ቢያቅተው፣

ኀጢአተኛዋ ምሕረትን አገኘሁ

ዕድፋሙን ታሪክ ሻርክልኝ እንዳልነበር፣

ምሕረትህ አወጣ ለሕይወቴ አዲስ ጀምበር

ታምር ነው፤ ተባልሁኝ እኔም የእግዚአብሔር ልጅ በደሌ ተሽሮ ተወግዶልኝ ፍርድ

በኢየሱስ ቤዛነት እኔም ገባሁ ከደጅ፤

በደሌ ተሽሮ ተወግዶልኝ ፍርድ

ምላሽ ‘ሚሆን አጣሁ ለውለታህ

ምን ደርሶ ጥግህ ላይ ምን ሊመጥንህ?

ደስ ካሰኘህ ሞልቶ በዐይንህ፣

ራሴን በመሠዊያው ላኑርልህ፤

ደስ ካሰኘህ ሞልቶ ባይንህ፣

በገዛ ዘመኔ ላገልግል ፈቃድህን

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ