የለሁበትም
Yelehubetm
5:19 · አማርኛ
ሁሌ የሚገርመኝ የሚደንቀኝ አንድ ነገር
ተጠቅልላ በምታልፍ ምድር መታሰቤ በእግዚአብሔር
እኔን የሚገርመኝ የሚደንቀኝ አንድ ነገር
ተጠቅልላ በምታልፍ ምድር መታሰቤ በእግዚአብሔር
ይህንን አይተ ይህንን ቆትረ ቢዬ ምለው ስለሌለኝ
እጄን በአፌ ጭናለሁ
ጸጋ ከመጠን አልፎ ምህረት ከሐጢያቴ ገዝፎ
በገዛ መንገዴ ስዳክር ሳብከኝ ወደ እረፍቴ በፍቅር
ዓለም ሳይፈጠር የወሰንከኝ የጸጋ ክብር እንዲመሰገን
ሁሉ ባንተ ካንተ ሆነልኝ ምን አዋጣሁኝ እንድትወደኝ
የለሁበትም ለመዳኔ
የለሁበትም ለመመረጤ
እጄ የለበትም ከሆነው ቸርነት
ስምህ ይባረክ ሁሉ ባንተ ምህረት
የለሁበትም ለመወደዴ
የለሁበትም ለመማሬ
እጄ የለበትም ከሆነው ቸርነት
ስምህ ይባረክ ሁሉ ባንተ ምህረት
አመሰግናለው አመሰግናለው
አመሰግናለው ሲገርመኝ ኖራለው
አመሰግናለው አመሰግናለው
አመሰግናለው ሲደንቀኝ ኖራለው
በመዳፍህ ሽንቁ በዛ የመስቀል ጣር
ተገኘች ሕይወቴ አምልጣ ከሞት ባህር
እኔ ተቀበልኩኝ በነጻ ድህነትህ
ዓብ ግን ከፍሎበት ነው አንዲያ ዉድ ልጁን
የለሁበትም ለመዳኔ
የለሁበትም ለመመረጤ
እጄ የለበትም ከሆነው ቸርነት
ስምህ ይባረክ ሁሉ ባንተ ምህረት
የለሁበትም ለመወደዴ
የለሁበትም ለመማሬ
እጄ የለበትም ከሆነው ቸርነት
ስምህ ይባረክ ሁሉ ባንተ ምህረት
አመሰግናለው አመሰግናለው
አመሰግናለው ስገዛ ኖራለው
አመሰግናለው አመሰግናለው
አመሰግናለው ሳመልክህ ኖራለው
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ