እጠብቅለሁ
Etebkhalew
አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የሙጥኝ ብዬ ናልኝ ባልኩህ ጉዳይ፣
“በስፍራሽ ጠብቂኝ እመጣለሁ” ባልከኝ፥
እኔ ያሰመርኩት የቆረጥሁት ቀን ቢያልፍ፣
ስፍራዬን ለቅቄ እንዳንተላለፍ፣
ትናንት ያ’ረግኸውን ታማኝነትህን፣
እጠብቃለሁ አስቤ እውነትህን፣
ታግሼ እውነትህን
አዝማች · Chorus
እጠብቅሀለሁ በስፍራዬ፣ እስክትመጣ ጌታዬ፣
እጠብቅሀለሁ ሳልላወስ፣ ጊዜህን በመታገሥ
ቁጥር 2 · Verse 2
“ዘርህን አበዛለሁ እንደ ሰማይ ከዋክብት፣
ተብለህ ትጠራለህ የአሕዛብ ሁሉ አባት”
ያልከው ቃል ቢዘገይ እስኪመስል የተረሳ፣
ወደ አጋር ገባ በእስማኤል ሊወሳ፣
ተስፋውን ሊጨብጥ በገዛ መንገዱ፣
ይስሐቅን ለማቀፍ ባቋራጭ ቢሄዱ፣
ከባሪያዪቱ አይደል የቃልኪዳን ልጅ፣
እግዚአብሔር ካየው ከነጻዪቱ እንጂ
በሰው ቀመር አይደል ምትመጣ ያንተ እጅ
አንተ በወደድከው ባንተው ሰዓት እንጂ
እንድጠብቅ ነቅቼ ተዘጋጅቼ፣
እንዳያዝንብኝ ልቤ እምነቴን አንግቤ፣
ጸጋህ ይርዳኝ እንድጸና እኔ የድርሻዬን፣
ሰማይ ምድር ቢያልፉ ይቀልላል፣
አንተማ ከምታጥፍ ቃልህን
እግዚአብሔር ቃሉን አያጥፍም፤
ይዋሽ ዘንድ ሰው አይደለም፤
ይመጣል እመጣለሁ ካለ፣
ዙሪያዬ ቢለኝ “የታለ?”
የተሰወርሁ አይደለሁም ከዐይኑ፣
አላለፈም የፍርዴም ሚዛኑ፣
በከንቱ አይደል ጥበቃዬ፣
ሁሉን መልካም ያደርጋል ጌታዬ
ነገዬን ሳቅ ያደርጋል ጌታዬ
አዝማች · Chorus
እጠብቅሀለሁ በምስጋና ትመጣለህና፣
እጠብቅሀለሁ በደስታ ታማኝ የኔ ጌታ፤
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ