እነግርሃለሁ
Enegrehalehu
5:17 · አማርኛ
ማንም ሳይነግርህ ሁሉን ብታውቅም፣
በልቤ ያለውን ከአንተ አልደብቅም
ማንም ሳይጠቁምህ ሁሉን ብታይም፣
የውስጤን እኔን ከአንተ አልሰውርም
ያየኸውን አሳይሃለሁ፤
ያወቅኸውን እነግርሃለሁ፤
ሸክሜ የሚቀለው ከእግርህ በታች ነው፤
ለአንተ ያሳየሁት ሁሉ መላ አለው፤
ላዬ ዝም ብሎ ውስጤ ግን ሲዋትት፣
ማንም ልብ እማይለው በሹክሹክታ ዐይነት፣ የውስጤን በውስጤ ነግሬህ በብርቱ፣
ሁሉ ደኅና ሆነ ሲደርስ ሰዓቱ
ለአንተ ስነግር ይቀለኛል፤
ከአንተ መማከር ይቀናኛል፤
ከአኔ እኩል አታይ የሕይወቴን ክስተት፣
ሁሉ ራቁት ነው፤ ግልጽ ነው በአንተ ፊት
እያየኸው አሳይሃለሁ፤
ያወቅከው እነግርሃለሁ፤
ሸክሜ የሚቀለው ከእግርህ በታች ነው፤
ለአንተ የሰጠሁት ሁሉ መውጫ አለው
ፊትህ እሆናለሁ የሆንሁትን፣
ጭንብል አላጠልቅ ማስመሰልን፣
ቀድሞም ዐይንህ ቃላቴን ዘልቆ፣
ይመረምራል የልቤን ጠልቆ
የጓዳዬ ምስጢረኛዬ
የምትሰማኝ ‘ምታደምጠኝ
‘ምትረዳኝ፣ ‘ምትረዳኝ
ነገሬን እግርህስር አምጥቼ እጥላለሁ
ላንተ የነገርኩ እለት ፈውሴን አገኛለሁ
የማላሳይህ፣ የማላዋይህ፣
‘ማላማክርህ፣ የማልነግርህ
ጉዳይ አለኝ ወይ?
የልቤ አምላክ ሆይ፤ ቅሩብ ለነፍሴ፣
ምን ነገር አለ የማስቀረው ብዬ በራሴ? (*2)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ