የማይለወጥ
Yemaylewet
5:09 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ዕድልን ሰጥተኸኝ ብኖር ብዙ ዘመን፣
በዕድሜዬ ማምሻ ኑሮዬ ሲመዘን፣
አንገት ‘ምደፋበት በሐፍረት የማስበው፣
ቀናት ዓመት አይኑር ታሪኬን ‘ሚያጎድፈው፤
መሻቴ በክብር ማብቃት ሩጫዬን፣
ታማኝ ባሪያ መባል፣ ከእጅህም አክሊሌን
አዝማች · Chorus
የማይለወጥ ልመናዬ፣
የማልሽረው ጽኑ መሻቴ፣
ሁሌም በቤትህ እንድኖር፤
እርምጃዬ ፊትህ እንዲያምር
ፍፃሜዬ ፊትህ እንዲያምር
ቁጥር 2 · Verse 2
ያልተመሠረተ ጸንቶ በዐለቱ፣
ንፋስ ጎርፍ ሲመጣ አሃሃ ታላቅ ነው ውድቀቱ
እስከ መኸር ቢዘልቅ እንክርዳድ ከስንዴው፣
አይገባ ጎተራ፣ አሃሃ በእሳት መደምደሚያው
አዝማች · Chorus
በፊትህ ጸሎቴ ሞገስ ያግኝ፤
በፍጻሜ ማማር እባክህ ባርከኝ (*2)
ቁጥር 3 · Verse 3
ድንገት ሄጄ ሄጄ ልቤ እንዳይከዳኝ፣
በሰው የጠላሁት በቤቴ እንዳይገኝ፣
የፈራሁት ያንን ሆኜው እንዳልገኝ፤
አዝማች · Chorus
ብርታቴ ሆይ፤ አንተ የማምለጫ ዐለቴ፣
ከጸጋህስ በቀር ምን ሊሆን ትምክህቴ? (*2)
ቁጥር 4 · Verse 4
ነፍሴ ስትዝል፣ ስትደክምብኝ፣
የኀጢአትን ጽዋ እንዳትጠጣብኝ፣
እስከ ሞት ታግሦ በአብ ቀኝ ያለውን፣
አስታውሳታለሁ የእምነቴን ራስ ፈጻሚው ኢየሱስን
ባክኖ እንደማይቀር ተጋድሎዬ መና፣
የአባቶች ምስክር ሆኖ እንደ ደመና፣
ያጽናናታል ነፍሴን የድል ታሪካቸው፣
በተስፋ የታገሡ ከእጁ ነው ዋጋቸው
አዝማች · Chorus
እስክትመጣ እስካይህ፣
እስክሸለም ከእጆችህ፣
በተስፋ ቃል እጽናናለሁ፤
በጸጋህም እመካለሁ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ