Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ኢየሱስ

Eyesus

5:40 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

የማይታይ አምላክ ምሳሌ፣

የአብ ማንነቱ ትንታኔ፣

ከፍጥረታት በፊት ነህ አልፋ፣

ሁሉ በአንተ ላንተ ነህ ዖሜጋ

አትመረመር ኢየሱስ ረቂቅ ነህ፤

ማን ያውቀዋል መንገድህን?

አትመረመር ኢየሱስ ረቂቅ ነህ፤

ከ እስከ የለው ዕድሜ ዙፋንህ!

ሳትመጣ ወደ ምድር ቃል ሥጋ ሆነህ፣

‘ምትመለክ በመንበርህ፣

ሳትታቀፍ በፊት በሰው እጅ ወርደህ፣

ዘላለማዊ ጅማሬ የሌለህ

ጎንህ ሳይወጋ ታዘህ ለመስቀል፣

ሁን ብለኸው ፍጥረት ተጋጥሟል፤

ሳታስታርቅ በሞት ሰማይን ከምድር፣

ክርስቶስ ኢየሱስ አንተ ወልድ እግዚአብሔር

አትመረመር ኢየሱስ ረቂቅ ነህ፤

ማን ያውቀዋል መንገድህን?

አትመረመር ኢየሱስ ረቂቅ ነህ፤

ከ እስከ የለው ዕድሜ ዙፋንህ!

ላለውና ለነበረው ለሚመጣው፣

ሁሉንም ጠቅልሎ ለሚገዛው፣

አለቅነት ሥልጣናት፣

ፍጥረት ሁሉ ይሰግዳል፤

ለእርሱ ጌትነት! (*2)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ