Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ትውልድ አለ

Tewled Ale

4:42 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ዘመን ሲያስብል “ድሮ ቀረ ክርስትና”

ምስሉ ጠፍቶ ደብዝዞ ከትላንና፣

ሆኖ ድብልቅ ሕዝብ መልኩ ያልጠራ፣

ግስጋሴው የሚያስፈራ

ግን እግዚአብሔር ስለ ስሙ ግድ ይለዋል፤

በዘመናት ያለ ምስክር ራሱን መች ይተዋል?

የቤቱ ባለቤት ርስቱን አይጥልም፤

ከተኩሎቹ መሀል በጎቹ አይጠፉትም

“ለእግዜር ትውልድ አይቅር ብለው የማሉ

መሠዊያን አፍርሰው ኪዳንን የተዉ

ነቢያትን አጠፉ በክፋት ዘመቻ

ተስፋ ቆርጫለሁ፤ ቀርቼ እኔ ብቻ!”

ኀይሉ ሁሉ ተሟጥጦ ለፈራው ኤሊያስ

ከሰማያት መጣ አምላካዊ መልስ

“ቅሬታ አለኝ ከትውልዱ፣

ለባዕዳን ያልሰገዱ፣

ጉልበታቸው ያልተበላ፣

‘ማያምራቸው ወደኋላ”

እንደ አብድዩ አሉ ወገን

‘ሚያስመልጡ ትውልድ በቁርጥ ቀን

እንደ ዮዳሄ አሉ አባቶች፣

የሚያወርሱ የአምላክ ሥርዐት

የቤቱ ባለቤት ርስቱን አይጥልም፤

ከተኩሎቹ መሀል በጎቹ አይጠፉትም

አለው ትውልድ ዛሬም፣

በድብልቅ ዘመን ያልተበራረዙ፣

በጠባቡ መንገድ እውነትን የያዙ፣

በሁለት ሀሳብ ‘ማያነክሱ፣

ዐመፃን እጅ ያልነሱ፣

በነፍሳቸው የቆረጡ፣

በጽድቅ ወንጌል ያልቀየጡ፣

አተኩረው ብድራትን፣

የናቁ ይህች ዓለምን፣

ተሥሎ መስቀል በልባቸው፣

የእግዜር ጠላት ጠላታቸው

አለው ዛሬም ትውልድ፣

ልገኝ እኔም ሲባል አንድ

አልቀር በትዝታ፣ አልኖርም በምኞት

ትናንት የነበረው እግዚአብሔር ምን ተስኖት!

ልሁን የክብር ዕቃ እንጂ ልገኝ እኔ፣

አለ ሕያው ክንዱ ዛሬም በዘመኔ

የእምነት ጋሻን አነሣለሁ

የመንፈስ ሰይፍ እመዝዛለሁ

እውነት ሆኖ ዝናሬ

በጽድቅ ወንጌል ጸንቶ እግሬ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ