Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አመልከዋለሁ

Amelkewalew

4:31 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ያወቅሁት እውነት ነጻ አውጥቶኛል፤

ልቤን አስከንድቶ በእምነት ያኖረኛል፤

ገብቶኛል የዘላለም ፍቅሩ፣

ተስፋ አለኝ ልካፈል ከክብሩ

አንዳንድ መንገዶቹ ባይገቡኝ፣

ባልገነዘበው ባይመስሉኝ፣

ለጊዜው መልስ ባጣ ባይብራራልኝ፣

ጨርሼ አላውቀው ረቂቅ እግዚአብሔር፣

ግን አያናጋውም የእምነቴን ማገር

ቀድሞንስ የምሸመድደው፣

ምኑን አምላክ ሊሆን መግቢያ መውጫውን ‘ማውቀዉ?

ግን ሳይለዋወጥ ማልዶ አዲስ እግዚአብሔር፣

ይህ ነው በመደነቅ ‘ሚያመጣኝ ከእግሩ ሥር

አመልከዋለሁ ተደስቼ፣

አምላክ በሆነኝ በእርሱ ረክቼ አሃ

አመልከዋለሁ ሳላቅማማ፣

እውነት ከእርሱ ወዲያ ሌላ የለማ!

እንድረዳው እንጂ እንደኔ ያከለው፣

ልኩ ሰው አይደለም፤ አምላኬ ትልቅ ነው

ሰማይ ዙፋኑ፣ መርገጫው ምድር፣

ሙሉ ራሱን ቢገልጥ ማን ይገባው ነበር?

“እርሱ ይህ ነው” የሚል አጥንቶ መርምሮ፣

ማን ተገኝቶ ያውቃል ከእጁ ሥራ አእምሮ?

በስሌት በቀመር ማንም አያገኘው፣

ራሱን ባይገልጥልን ሰው አይደርስበትም

አመልከዋለሁ ተደንቄ፣

ጨርሼ ስለርሱ እንደማላውቅ አውቄ፤ አሃ

አመልከዋለሁ እጄን ባፌ ጭኜ፣

ከመታወቅ የሚያልፍ መሆኑን አምኜ

ያሁን በድንግዝግዝ ጥቂት ዕይታዬ፣

ፍጹሙ ሲመጣ ይጠራል ብዥታዬ

ዛሬ እንደ ብልጭታ ጥቂቱ ዕይታ፣

ፍጹሙ ሲመጣ ይሆናል ወገግታ

አመልከዋለሁ ተደስቼ፣

አምላክ በሆነኝ በእርሱ ረክቼ አሃ

አመልከዋለሁ ሳላቅማማ፣

እውነት ከእርሱ ወዲያ ሌላ የለማ!

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ