Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አንደበት

Andebet

4:39 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

አንደበት እሳትን ነው በጉያው ያቀፈው፣

‘ሚገድል እሚያድን ፍጹም ኀይል ያለው፤

ሞትና ሕይወት በምላስ እጅ

ሁለት ጽንፍ ፍሬ፣ ጽድቅ ወይ ኩነኔ

ከዚህችው አንድ እኔ

በዚያች ሰማሪያ ጽኑ ረሀብ ገብቶ፣

“ነገ ጥጋብ ነው” ቢል ባሪያው ከአምላኩ ሰምቶ፣

“ይህ እንዴት ይሆናል ቢከፋፈት ሰማይ?

የችግሩ ጥልቀት የሚታይ አይደል ወይ?”

የንጉሥ ጥበቃ በእምነት ቃል ዘበተ፤

የልቡ ስንፍና አፉን አስከፈተ

እ’ሱ ብቻ ነው ወይ ያላመነው ከሁሉ፣

ጥፋት ደጁን ማሰ፤ አንደበቱን ባለመከልከሉ፤

ምርኮን አይቶ ሳይቀምስ ተረጋግጦ ሞተ

ምን ነበር ዝም ቢል? ባፉ ባልዘመተ?

ባልገባኝ ነገር ላይ ዝም እላለሁ፤

አንደበቴን ከፍርድ እከለክላለሁ፤

ነፍሴ እንዳትዋጥ በመከራ

ሕግህ ዘወትር እኔነቴን ይግራ

አንደበቱን የሚጠብቅ፣

ንግግሩን የሚያርቅ፣

ከተማን ከሚመራ፣

ይበልጣል መንፈሱን ‘ሚገራ

ዘመን አይቶ አስተዋይ ዝም ይላል፤

ከፍርድ መንበር እራሱን ይገታል፤

ለሁሉ ጊዜ እንዳለው አውቆ፣

ይኖራል ሚዛኑን ጠብቆ

የሰው ቁጣ ላይሠራ የአምላክ ጽድቅ፣

ሥጋ ለባሽ ለራስ ፍርድ አይታጠቅ፣

የእውነት ዳኛ አለ በዙፋኑ፣

በፍርድ ያልፋል በጊዜ ሚዛኑ፣

አያደላ ብያኔው የእውነት፣

በጽድቅ ነው የእርሱ ዳኝነት

ቃል እንደ ሰይፍ ነው፤ ጠልቆ ልብ ይወጋል፤

የአንደበት ቁስል ፈጥኖ መች ይጠግጋል ?

በልብ ሀሳብ ሞልቶ በአንደበት ጎርፎ፣

ሩጫ ሳይቃጠል ጽድቅ እንነጋገር

ዝም እላለሁ ለሁሉ ጊዜ አለው፤

ከፍርድ መንበር ምላሴን እገታለሁ

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ