Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ብልህ ሰው ነፍሱን ያድናል

Beleh Sew Nefsun Yadenal

1980 · ትራክ 4 · 2:41 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ጌታ ሆይ ከሞት ሕይወት ይመረጣል

ብልህ ሰው ነፍሱን ያድናል

በስምህ ትዕዛዝ ስር ያድራል

በልቡ አንተን ፈላጊ

ስምህን ጠሪ ይባረካል

በኑሮ የሚያስቀድምህ

የደስታን ካባን ይደርባል

ከእርኩሰት ታርቀዋለህ

በልቡ ዙፋን ላይ ነግሰህ

ሰላምን በውስጡ አኑሮ

ይጓዛል ደስታን ጨምሮ

ጌታ ሆይ ከሞት ሕይወት ይመረጣል

ብልህ ሰው ነፍሱን ያድናል

በስምህ ትዕዛዝ ስር ያድራል

ከኋለኛው ሃዘን ይልቅ

የአሁኑን ጉስቁልና መርጦ

ጊዜያዊውን ተድላ ንቆ

ነፍሱን ከሥጋው ያየ አብልጦ

ብልህ ነው ጠቢብ አዋቂ

የሰማይ ሃገር ዘላቂ

ዘለዓለም እረፍትን አይቷል

ለተስፋው ምድር ተመርጧል

ጌታ ሆይ ከሞት ሕይወት ይመረጣል

ብልህ ሰው ነፍሱን ያድናል

በስምህ ታዛ ስር ያድራል

በለመለመ መስክ አድሮ

የጠራ ምንጭ ውኃ ጠጥቶ

በአምላኩ እንክብካቤ አድርጐ

መጓዙን የሰው ልጅ አጥላልቶ

ከስታለች ተርባ ነፍሱ

ታውኳል ሥጋ መንፈሱ

ይመለስ ሚወድ ይመለስ

ሳይወድቅ ጉልበቱ ሳይፈር

ጌታ ሆይ ከሞት ሕይወት ይመረጣል

ብልህ ሰው ነፍሱን ያድናል

በስምህ ታዛ ስር ያድራል (፬x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ