Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ማረኝ አቤቱ

Maregn Abietu

1980 · ትራክ 7 · 6:04 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ማረኝ ጌታ ሆይ

ማረኝ አቤቱ ከመዓቱ (፪x)

እንደሎጥ አድነኝ እንደኖህ አድነኝ

አንደበቴ ረክሶ ሰላሜን ነጠቀኝ

ስንዴነቴን እንጃ እንክርዳድ ብቻ ነኝ (፪x)

ማረኝ ጌታ ሆይ

ማረኝ አቤቱ ከመዓቱ (፪x)

ጌታ ሆይ አየሁኝ ጊዜ ያሳይ የለ

ያ ሁሉ ግለቴ??? ተሟጦ የታለ

ቀኑን ሙሉ ልቤ አንተን እንዳላለ (፪x)

ማረኝ ጌታ ሆይ

ማረኝ አቤቱ ከመዓቱ (፪x)

ቃልህን ህግህን እግሬ ስር ጥያለሁ

እንደ ሥጋ ፈቃዴም እመላለሳለሁ

ማረኝ እንደገና እማጸንሃለሁ (፪x)

ማረኝ ጌታ ሆይ

ማረኝ አቤቱ ከመዓቱ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ