መንገዴን በፊቱ አጸናለሁ
Megedien Befitu Atsenalehu
1980 · ትራክ 3 · 4:02 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ነገር ግን መንገዴን በፊቱ አጸናለሁ
ቢገድለኝም እንኳን እርሱን ጠብቃለሁ
እርሱን ጠብቃለሁ ጠብቃለሁ ጠብቃለሁ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
የሆነው ነገር ይምጣብኝ ሥጋዬን በጥርሴ እይዛለሁ
ቢገድለኝ እንኳን ታግሼ ሕይወቴን በእጁ አኖራለሁ
መድሃኒት ይሆንልኛል ነገሩ አይመረመርም
እጠብቀዋለሁ ጌታን በጥቂቱ ዝዬ አልወድቅም
አዝማች · Chorus
ነገር ግን መንገዴን በፊቱ አጸናለሁ
ቢገድለኝም እንኳን እርሱን ጠብቃለሁ
እርሱን ጠብቃለሁ ጠብቃለሁ ጠብቃለሁ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በለስ እንኳን ባታፈራ የወይን ሃረግ ቢደርቅ
ዝም ብዬ የጌታን ቀን በትዕግሥት ልጠብቅ
የወራት ስራ ቢጐድል እርሾቼም ባያበሉኝ
እግዚአብሔር ኃይሌ ይሆናል ጥሩ ሰዓት ሲወጣልኝ
አዝማች · Chorus
ነገር ግን መንገዴን በፊቱ አጸናለሁ
ቢገድለኝም እንኳን እርሱን ጠብቃለሁ
እርሱን ጠብቃለሁ ጠብቃለሁ ጠብቃለሁ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በውስጤ ስላደረው ተስፋ መንፈሱ አያሳፍረኝም
እንደ ኢዮብ ሳያጽናናኝ እግዚአብሔር ከቶ አይተወኝም
ከጋጣዬ የጠፉት ላሞች ነገ ይበራከታሉ
ያላገጡብኝ ጠላቶች የአምላኬን ስራ ያያሉ
አዝማች · Chorus
ነገር ግን መንገዴን በፊቱ አጸናለሁ
ቢገድለኝም እንኳን እርሱን ጠብቃለሁ
እርሱን ጠብቃለሁ ጠብቃለሁ ጠብቃለሁ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ