የንጋቱ ኮከብ አበራ
Yenegatu Kokeb Abera
1980 · ትራክ 5 · 4:28 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
የንጋቱ ኮከብ አበራ
ጌታ ኢየሱስ በሁሉም ስፍራ
ማን ያግደው ማን ይታገለው
ይቆራርጣል ቃሉ ሰይፍ ነው
ማን ያግደው ማን ይታገለው (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
በዓለም ነግሰው ኃያል ነን ያሉት
ትንሳኤህን ሽረው ሞትህን ሊያስወሩ
ብዙ ለፉ ላይሆንላቸው
ጌታ ኢየሱስ አሸነፋቸው (፪x)
አዝማች · Chorus
የንጋቱ ኮከብ አበራ
ጌታ ኢየሱስ በሁሉም ስፍራ
ማን ያግደው ማን ይታገለው
ይቆራርጣል ቃሉ ሰይፍ ነው
ማን ያግደው ማን ይታገለው (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በእሳት በውኃ የእግዚአብሔርን ቃል
ከምር ሊያጠፋ እጅግ አልሟል
የምስራቹ አንዳይሰማ
ጠላት ጣረ በጭፍራው አድማ (፪x)
አዝማች · Chorus
የንጋቱ ኮከብ አበራ
ጌታ ኢየሱስ በሁሉም ስፍራ
ማን ያግደው ማን ይታገለው
ይቆራርጣል ቃሉ ሰይፍ ነው
ማን ያግደው ማን ይታገለው (፪x)
የንጋቱ ኮከብ አበራ
ጌታ ኢየሱስ በሁሉም ስፍራ
ማን ያግደው ማን ይታገለው
ይቆራርጣል ቃሉ ሰይፍ ነው
ማን ያግደው ማን ይታገለው (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ነገሥታቶች ሰይፍ መዘዙ
ገናና ሆነው ምድርን ሊገዙ
ኢየሱስ ግን ከአሪያም ተቀምጦ
ሁሉን ገዛ ታሪክ ለውጦ (፪x)
አዝማች · Chorus
የንጋቱ ኮከብ አበራ
ጌታ ኢየሱስ በሁሉም ስፍራ
ማን ያግደው ማን ይታገለው
ይቆራርጣል ቃሉ ሰይፍ ነው
ማን ያግደው ማን ይታገለው (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ