Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ሰላም አለኝ

Selam Alegn

1980 · ትራክ 10 · 6:19 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ቅብዝብዝነትን አጣሁት ከላዬ

መንፈስ ቅዱስ ገዛው ዘልቆ ልቦናዬን

ኃይልን ከአርያም መልበሴን የማውቀው

የማያልፍ ሰላም ስላልተለየኝ ነው

ሰላም አለኝ እንደወንዝ እንደወንዝ የሚፈስ

አዕምሮዬን የሚያረሰርስ

ደስታ አለኝ ከውስጤ ከውስጤ ማይጠፋ

ኢየሱስ ክብሩ ይስፋ ኡ.... (፪x)

ማነው የሚነጥቀኝ ይህንን ጸጥታ

የማይለየኝ ከውስጤ ለአንድ አፍታ

ከሰማይ ተገኝቶ ሰማያዊ የሆነ

ምድራዊማ ይሄኔ ትቶኝ በተነነ

ሰላም አለኝ እንደወንዝ እንደወንዝ የሚፈስ

አዕምሮዬን የሚያረሰርስ

ደስታ አለኝ ከውስጤ ከውስጤ ማይጠፋ

ኢየሱስ ክብሩ ይስፋ ኡ.... (፪x)

እግዚአብሔር ይመስገን እንቅልፌን እተኛለሁ

አደራዬን ለእርሱ ለአምላኬ እጥላለሁ

የብረት መዝጊያዬ ኢየሱስ ሆኖልኛል

በእርሱ ተሸሽጌ ምንስ ይደፍረኛል

ሰላም አለኝ እንደወንዝ እንደወንዝ የሚፈስ

አዕምሮዬን የሚያረሰርስ

ደስታ አለኝ ከውስጤ ከውስጤ ማይጠፋ

ኢየሱስ ክብሩ ይስፋ ኡ.... (፪x)

ጌታ መሰረቴ የማይነቃነቅ

ድጋፍ መጽንናኛዬ የሚያነሳኝ ስወድቅ

መናወጥ ከልቤ ጠፍቷል ላይመለስ

የሰላሜ ጌታ ይመስገን ኢየሱስ

ሰላም አለኝ እንደወንዝ እንደወንዝ የሚፈስ

አዕምሮዬን የሚያረሰርስ

ደስታ አለኝ ከውስጤ ከውስጤ ማይጠፋ

ኢየሱስ ክብሩ ይስፋ ኡ.... (፫x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ