Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

መዳን ይሆንልናል

Medan Yehonelenal

1980 · ትራክ 8 · 3:15 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ለእኛስ ከሌላ ስፍራ መዳን ይሆንልናል (፪x)

በዓለም ምናምን ተስፋ አድርገን

ልባችን ረግቶ እፎይ ብለን

መኖር እንድንችል ብዙ ረባን

ሁሉ ግን ደቆ ኢየሱስ ቀረን

ለእኛስ ከሌላ ስፍራ መዳን ይሆንልናል (፪x)

ወደ ተራራው በሮ ዓይናችን

ሊያገኝ ሮጦ መድሃኒትን

ሲማትር ከርሞ ወንዝ ሜዳውን

ኋላ ቆይ አለ ሲያይ እግዚአብሔርን

ለእኛስ ከሌላ ስፍራ መዳን ይሆንልናል (፪x)

ዛፉን ቅጠሉን እንስሳውን

ኃይለኛ አዋቂን ባለጸጋን

ጥበብና ዕውቀት ፍልስፍናን

ተስፋ ያደረግን ሞትን ተጐዳን

ለእኛስ ከሌላ ስፍራ መዳን ይሆንልናል (፪x)

ኋላ መለስ አልን ሮጠን ሮጠን

በሙላት ጋበዝን ኢየሱስ ጌታን

ካለሰብንበት መልስ አገኘን

ለዘለዓለም ክብር ይሁን

ለእኛስ ከሌላ ስፍራ መዳን ይሆንልናል (፫x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ