እንደ ሌባ
Ende Lieba
1980 · ትራክ 14 · 3:05 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
እንደ ሌባ እንደ ወንጀለኛ
ንጹህ አምላክ ሆነልን ስለእኛ
በጨለማ በድቅድቁ ሳለን
በእግዚአብሔር ኢየሱስን አገኘን (፪x)
እጅግ ከብዶት ነበረ መስቀሉ
አሸክመው ሲያስጨንቁት ዋሉ
ለዓለም ኃጢአት ኢየሱስ ተመታ
በመስቀል ሞት በእርባን እንዲፈታ (፪x)
የደሙ ላብ አለዋጋ አይደለም
የጐኑ ውኃ ለከንቱ አልፈሰሰም
ንጹህ ደሙ ለእንስሳት አይደለም
ክቡር ማንጻት አለው ለእኔም ለአንተም (፪x)
አዝማች · Chorus
እንደ ሌባ እንደ ወንጀለኛ
ንጹህ አምላክ ሆነልን ስለእኛ
በጨለማ በድቅድቁ ሳለን
በእግዚአብሔር ኢየሱስን አገኘን (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ