ትህትና ሊያስተምረኝ
Tehetena Liyastemregn
1980 · ትራክ 11 · 3:53 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ትህትና ሊያስተምረኝ ወዶ
እግር አጠበ ባርያውን ወርዶ
እራሱን አዋርዶ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ደቀ መዛሙርቱ አግራቸው ቆሸሸ
አደፈ ጐደፈ ፍፁም ተበላሸ
ሁሉን የፈጠረ ሰውን የወደደ
ጭቃውን ሊያስወግድ ወደታች ወረደ
አዝማች · Chorus
ትህትና ሊያስተምረኝ ወዶ
እግር አጠበ ባርያውን ወርዶ
እራሱን አዋርዶ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እርሱ ያላጠበው ከእርሱ ጋር አይኖርም
አይቆርስም ከአምላክ ጋራ አንድነት የለውም
ጴጥሮስ ይህን አይቶ ሰውነቴን ደግሞ
እጠበኝ ጌታ ሆይ አለውም ተማጽኖ
አዝማች · Chorus
ትህትና ሊያስተምረኝ ወዶ
እግር አጠበ ባርያውን ወርዶ
እራሱን አዋርዶ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
በሚደነቅ ብርሃን የሚኖር ፈጣሪ
አልፋና ኦሜጋ የፍጥረታት ሰሪ
ማበሻ ጨርቅ ወስዶ እግር ሊያጥብ ወረደ
ዝቅ አደረገ እራሱን ለሰው አዋረደ
አዝማች · Chorus
ትህትና ሊያስተምረኝ ወዶ
እግር አጠበ ባርያውን ወርዶ
እራሱን አዋርዶ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
የሁሉ ማሰሪያ አላማ ያለው ነው
ጌታ ይህን አድርጓል እኔስ እንደምነው
የወንድሜን እግር እስካጥብ ዝልቅ ካልኩ
እውነትም ኢየሱስን በእርግጥ ተከተልኩ
አዝማች · Chorus
ትህትና ሊያስተምረኝ ወዶ
እግር አጠበ ባርያውን ወርዶ
እራሱን አዋርዶ (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ባሪያ ከሚያኖረው አይበልጥም አላቸው
መልዕክተኛም አይበጅ ይልቁን ከላከው
እንግዲህ ጌታችሁ እኔ ይህን ስፈጽም
አድርጉት ለሁሉም ዛሬ ሁኑ እናንተም
አዝማች · Chorus
ትህትና ሊያስተምረኝ ወዶ
እግር አጠበ ባርያውን ወርዶ
እራሱን አዋርዶ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ