Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ዘመኑ አስፈሪ ቢሆንም

Zemenu Asferi Bihonem

1980 · ትራክ 15 · 4:14 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ዘመኑ አስፈሪ ቢሆንም

የጌታ ፀጋ አላነሰንም

ዲያቢሎስ ቢራቀቅ ቢመጥቅ

አይተኛም እኛን የሚጠብቅ (፪x)

እርግጥ ነው ጠላታችን እጅግ ተራቋል

መጠላለፊያውን ሰውሮ አስቀምጧል

ምድርን በእጁ አድርጐ ይጫወትባታል

ለእኛ ግን እግዚአብሔር እንዳለን ተረድቷል

ዘመኑ አስፈሪ ቢሆንም

የጌታ ፀጋ አላነሰንም

ዲያቢሎስ ቢራቀቅ ቢመጥቅ

አይተኛም እኛን የሚጠብቅ (፪x)

ሃያ እጥፍ ቢያነድም እሳቱን ሊያስበላን

የሚያጠውፋው ውኃ ኢየሱስ አለልን

ባህሩን ቢያሰፋ ሊያሰምጠን ወደስር

መርከብ ሆኖ ማዶ አለን የሚያሻግር

ዘመኑ አስፈሪ ቢሆንም

የጌታ ፀጋ አላነሰንም

ዲያቢሎስ ቢራቀቅ ቢመጥቅ

አይተኛም እኛን የሚጠብቅ (፪x)

ምድርን ለቆ ሰይጣን በአየር እየሮጠ

ሊያዳክም የአማኝን በሩን ቀጠቀጠ

የክርስቲያን መዝጊያው አይበገር ኖሮ

መና ቀረ ጠላት ያለ ኃይሉን ጥሎ

ዘመኑ አስፈሪ ቢሆንም

የጌታ ፀጋ አላነሰንም

ዲያቢሎስ ቢራቀቅ ቢመጥቅ

አይተኛም እኛን የሚጠብቅ (፪x)

ወጥመዱ በርትቶ ሊያጠምደን ቢጣጣር

ሕያው አምላካችን ይዋጋል ከእኛ ጋር

የጽዮን አርበኛ ቆራጥ የታጠቀ

አንዴም አልተረታ አንዴም አልወደቀ

ዘመኑ አስፈሪ ቢሆንም

የጌታ ፀጋ አላነሰንም

ዲያቢሎስ ቢራቀቅ ቢመጥቅ

አይተኛም እኛን የሚጠብቅ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ