እኔስ በሕይወቴ ልበርታ
Enies Behiwotie Leberta
1980 · ትራክ 12 · 4:44 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
መሰረቴ ጠብቆ ብጓዝ እወዳለሁ
አለዚያ በንፋስ እወዛወዛለሁ
እንደኔማ እንደሃሳቤ
ድል ተሞልቶ ባየሁ ልቤን (፪x)
አዝማች · Chorus
እኔስ በሕይወቴ ልበረታ
ምኞቴ ነው ጠዋት ማታ
ለጥሞና ጊዜ አጣሁኝ
ዘወትር በውጊያ ላይ እያለሁኝ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ማጉረምረምን ቀርቶ ምሥጋና ዘለዓለም
በደስታ ሰሞን በስቃይ ቢሆንም
ይህን ነበር የምመኘው
ውጊያ በዝቶ የት ላግኘው (፪x)
አዝማች · Chorus
እኔስ በሕይወቴ ልበረታ
ምኞቴ ነው ጠዋት ማታ
ለጥሞና ጊዜ አጣሁኝ
ዘወትር በውጊያ ላይ እያለሁኝ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
መብራት እየበራ ውስጤ ገብቶ ኢየሱስ
ንጹህ ቦታ አግኝቶ ቢኖር መንፈስ ቅዱስ
ይህን ነበር የምመኘው
ውጊያ በዝቶ የት ላግኘው (፪x)
አዝማች · Chorus
እኔስ በሕይወቴ ልበረታ
ምኞቴ ነው ጠዋት ማታ
ለጥሞና ጊዜ አጣሁኝ
ዘወትር በውጊያ ላይ እያለሁኝ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ቅድስና ሞልቶባቸው ሁሉም ብልቶቼ
በኑሮዬ በጌታ ግን ሥጋዬን ገዝቼ
ልኖር ነበር የምመኘው
ውጊያ በዝቶ የት ላግኘው (፪x)
አዝማች · Chorus
እኔስ በሕይወቴ ልበረታ
ምኞቴ ነው ጠዋት ማታ
ለጥሞና ጊዜ አጣሁኝ
ዘወትር በውጊያ ላይ እያለሁኝ (፫x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ