Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ሁሉን አየነው

Hulun Ayenew

1980 · ትራክ 13 · 3:59 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

በሚያስፈራው ዘመን ዙሪያው በተዘጋ

ቆምን ከእርሱ ጋር

እኛም ተቆረጥን ብለን ነበር ከድሞ

ኢየሱስ ዋጀን ደግሞ (፬x)

ሁሉን አየነው

ሁሉን አለፍን

ጌታን መረጥን

በእርሱ ላይ ቆመን ቆምን (፪x)

ዓይናችን ማየቱን አቁሞ ነበረ

ፍፁም ታወረ

እግራችን መሄዱን ተሳሰረ አበቃ

በፈተና ሲቃ (፬x)

ሁሉን አየነው

ሁሉን አለፍን

ጌታን መረጥን

በእርሱ ላይ ቆመን ቆምን (፪x)

በቃ ይታለፋል ያ ሁሉ በረሃ

በሌለበት ውኃ

እግዚአብሔር እርካታ ይሆናል ለደሃ

በሌለበት ውኃ (፬x)

ሁሉን አየነው

ሁሉን አለፍን

ጌታን መረጥን

በእርሱ ላይ ቆመን ቆምን (፪x)

ዮርዳኖስ ሲሞላ ልብ ስንጥቅ ሲል

ኢየሱስ ያግዛል

ባሕሩን ሰንጥቆ ሰላምን መስርቶ

ያሻግራል ማዶ (፬x)

ሁሉን አየነው

ሁሉን አለፍን

ጌታን መረጥን

በእርሱ ላይ ቆመን ቆምን (፪x)

ሁሉን አየነው

ሁሉን አለፍን

ጌታን መረጥን

በእርሱ ላይ ቆመን ቆምን (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ