እግዚአብሔር ሰውን ቢሆን
Egziabhier Sewen Bihon
1980 · ትራክ 2 · 3:18 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
እግዚአብሔር ሰውን ቢሆን
ከቶ ምን በዋጠን
ምስኪን የሚያጽናና አምላክ ነውና (፪x)
ወዳጄ መስሎ ጠላት
ገብቶ በደከምኩበት
አቆሰለኝ አድብቶ
ጥርሱን አሳይቶ (፪x)
ፊት አይቶ አያደላ
አምላክ የደሃ ጥላ
ሁሉም እኩል ነው ለእርሱ
ሥጋ ለባሽ ሁሉ (፪x)
ተመስገን ተመስገን እግዚአብሔር ተመስገን
የወደቅን እኛን ሰው አደረከን
የወደቅን እኛን ክብር አለበስከን (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ