ድንቅ ሥራ
Denq Sera
1980 · ትራክ 1 · 2:53 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ኮረብታውን ወጥቼ እፎይ አልኩኝ
ድንቅ የሆኑ ፍጥረታትን እያየሁኝ
ብቻዬን ነኝ ለማለት አልደፈርኩም
በዙሪያዬ አጫዋች አላጣሁም
አዝማች · Chorus
ድንቅ ስራ የአምላክ ስራ አይወራ
ድንቅ ስራ የአምላክ ስራ አይወራ
ቁጥር 2 · Verse 2
ቀስ እያልኩኝ ቀጠልኩኝ እርምጃዬን
አቤት ወፎች ከበውኛል ዙሪያዬን
ልዩ ልዩ ቀለም ለብሰው ሲጫወቱ
ደስ ያሰኛል የአምላክ ጥበብ መሰረቱ
አዝማች · Chorus
ድንቅ ስራ የአምላክ ስራ አይወራ
ድንቅ ስራ የአምላክ ስራ አይወራ
ቁጥር 3 · Verse 3
ሽው እያለ በሚያዝናናኝ ነፋስ ደግሞ
ሲወዛወዝ የ. (1) . አንገት ዘሞ
አንዴ ቀና አንዴ ጐንበስ አቤት . (2) .
እንዴት ሰራው ታላቅ ጌታስ ያሰኛል
አዝማች · Chorus
ድንቅ ስራ የአምላክ ስራ አይወራ
ድንቅ ስራ የአምላክ ስራ አይወራ
ቁጥር 4 · Verse 4
የአበቦቹ መዓዛ እያወደኝ
ልዩ ቃና ለአካላቴ እየሰጠኝ
በአምላክ እጆች በተሰሩት ተደንቄ
ተመለስኩኝ ወደ ቤቴ ብዙ አውቄ
አዝማች · Chorus
ድንቅ ስራ የአምላክ ስራ አይወራ
ድንቅ ስራ የአምላክ ስራ አይወራ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ