በመዝሙር ውዳሴ
Bemezmur Wedasie
1987 · ትራክ 4 · 4:02 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ቀናትም ያልፉና ዘመን ተፈፅሞ
የክርስቲያን ፈተና በምድር ላይ አክትሞ
በጥፋት ዓለም ውስጥ መኖር ያበቃና
የዓይናችንን እንባ ጌታም ይጠርግና
አዝማች · Chorus
በመዝሙር ውዳሴ በቅኔ ምሥጋና
በአሥራ ሁለት አውታር በታላቅ በገና ምሥጋና እንልና
ዕልልታው ሽብሸባው በዚያው ይደምቅና
መቼ ቀኑ ደርሶ ጌታም ይከብርና ምሥጋና
ቁጥር 2 · Verse 2
መች ይላል ተመሥገን ጊዜው ይደርስና
ከልቡ አልቅሶ ለጌታው ይነግርና
ምኞቱም ጥረቱም መቼ ይሳካና
ጌታን ሲል ይሰማል ልጄ ሆይ ተፅናና
አዝማች · Chorus
በመዝሙር ውዳሴ በቅኔ ምሥጋና
በአሥራ ሁለት አውታር በታላቅ በገና ምሥጋና እንልና
ዕልልታው ሽብሸባው በዚያው ይደምቅና
መቼ ቀኑ ደርሶ ጌታም ይከብርና ምሥጋና
ቁጥር 3 · Verse 3
አእላፋት ፃድቃን ከምድር እንሄድና
ነጭ ልብሳችን ለብሰን ዙፋን እንከብና
ኪሩቤል ላይ ላለው ለበጉ እንሰግድና
መች እንዘምር ይሆን ለኢየሱስ ምሥጋና
አዝማች · Chorus
በመዝሙር ውዳሴ በቅኔ ምሥጋና
በአሥራ ሁለት አውታር በታላቅ በገና ምሥጋና እንልና
ዕልልታው ሽብሸባው በዚያው ይደምቅና
መቼ ቀኑ ደርሶ ጌታም ይከብርና ምሥጋና
ቁጥር 4 · Verse 4
የምድር መፃተኛ ልብህ የተሰቀለ
ሰማያትን ለማየት ተስፋ ያልጐደለህ
መቼ ቀን ሞልቶልን ፅዮን ትደርስና
ጌታን በዓይንህ አይተህ ልብህ ይረካና
አዝማች · Chorus
በመዝሙር ውዳሴ በቅኔ ምሥጋና
በአሥራ ሁለት አውታር በታላቅ በገና ምሥጋና እንልና
ዕልልታው ሽብሸባው በዚያው ይደምቅና
መቼ ቀኑ ደርሶ ጌታም ይከብርና ምሥጋና
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ