Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ለፍቅር ትርጉም

Lefeqer Tergum

1987 · ትራክ 3 · 2:59 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ፍቅሩ የማያቋርጥ ጅረት ነው

አጥንትን ዘልቆ የሚሰማ

ልዩ ጣዕምም የሞላው

የብርታት ቅኔ የሚያሰማ

1.ፍቅርን ሳስባት ጌታ ኢየሱስን አልማለሁ

መላ አካላቴን አየዋለሁ

ፍቅሩ ሆን በውስጥ እረዳለሁ

የፍቅር ትርጉም እንደ ኢየሱስ የለም

2. ነፍስን ከመስጠት የበለጠ መውደድ የለም

ይህቺ ናትና ፍቅርም

ብርሃን የሆነች ለዚህ ዓለም

ፍቅርን ለማይት

ኢየሱስን መመልከት

አዝ፦ ፍቅሩ የማያቋርጥ ጅረት ነው

አጥንትን ዘልቆ የሚሰማ

ልዩ ጣዕምም የሞላው

የብርታት ቅኔ የሚያሰማ (፪x)

3. በወልድ ልብ ውስጥ ያለች ፍቅር ነች ፍጹሚቱ

የገለጸልን በሞቱ

ያልተለወጠች በእርዛቱ

ፍቅርን ለመቅመስ

በኢየሱስ መታደስ

አዝ፦ ፍቅሩ የማያቋርጥ ጅረት ነው

አጥንትን ዘልቆ የሚሰማ

ልዩ ጣዕምም የሞላው

የብርታት ቅኔ የሚያሰማ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ