ድል በድል
Del Bedel
1987 · ትራክ 13 · 2:37 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ድል በድል ጐዳና (፪x)
ክርስቲያን አሸነፈ እየሱስ አለውና (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ያን ድቅድቅ ጨለማ የሞትን ሸለቆ
ታገለው ክርስቲያን የእምነት ትጥቁን ታጥቆ
አሻፈረኝ ብሎ ለእርሱ ላይረታ
በድል ጥሎት ወጣ በጌታው መከታ
አዝማች · Chorus
ድል በድል ጐዳና (፪x)
ክርስቲያን አሸነፈ እየሱስ አለውና (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የጢሻን ጨለማ ብርሃን ወጣበት
ክርስቲያን በእምነት ሰይፍ አንዴ ቢዘምትበት
የማጥመጃ ሜዳ በደም አጥለቅልቆ
ሕያው ዘር ዘራበት እንዲበቅል አውቆ
አዝማች · Chorus
ድል በድል ጐዳና (፪x)
ክርስቲያን አሸነፈ እየሱስ አለውና (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ጋሻ ጦሩን መንፈስ ፍላጻው እምነቱ
ማን ሊቋቋመው ነው ያንን ክንደ ብርቱ
ሊያጠምዱት ቢያስቀሩት አጥብቀው ቢጥሩም
ከአምላኩ ደም ቅጥር አልነቀለም እግሩን
ቁጥር 4 · Verse 4
ድል በድል ጐዳና (፪x
ቁጥር 5 · Verse 5
ክርስቲያን አሸነፈ እየሱስ አለውና (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ