እንባዬን አፈሳለሁ
Enbayien Afesalehu
1987 · ትራክ 5 · 4:08 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በሥጋና በነፍስ ላይ ለሚሆን ፈተና
ሁሉንም የሚያስችለኝ መንፈስ ስጠኝና
እንደፈቀድክ አድርገኝ ሕይወቴን እመናት
ብትወድ ላመስግንህ ቢከፋኝም ላልቅስ
አዝማች · Chorus
በክብር ፀባዖቱ ገናናው ዙፋን ሥር ካለው
ፅዋዬም በፊትህ ሞልቶ ተርፎ ሳየው
እንባዬን አፈሳለሁ በምሥጋናም በለቅሶም
አምላኬ በቃህ እስኪለኝ ዓይኖቼን አብሶ
ቁጥር 2 · Verse 2
የእንባ ወንዛ ወንዝ አባቴ ነህ እያልኩ
ዳዊት በምሥጋና ሲስቅ ሲመላለስ
ሁሉን እንዳመሉ ጌታ ችለኸዋል
ባለቅስም ብስቅ አቅሜን አውቀኸዋል
አዝማች · Chorus
በክብር ፀባዖቱ ገናናው ዙፋን ሥር ካለው
ፅዋዬም በፊትህ ሞልቶ ተርፎ ሳየው
እንባዬን አፈሳለሁ በምሥጋናም በለቅሶም
አምላኬ በቃህ እስኪለኝ ዓይኖቼን አብሶ
ቁጥር 3 · Verse 3
ሊመጣ ካለው ክብር ይህን ሳወዳድር
የምሥጋናዬንም የለቅሶዬም ዝርዝር
እኩያ የለውም ምጻቱ የሚለው
ሁሉን አየዋለሁ ኢየሱስ ሲመለስ
አዝማች · Chorus
በክብር ፀባዖቱ ገናናው ዙፋን ሥር ካለው
ፅዋዬም በፊትህ ሞልቶ ተርፎ ሳየው
እንባዬን አፈሳለሁ በምሥጋናም በለቅሶም
አምላኬ በቃህ እስኪለኝ ዓይኖቼን አብሶ
ቁጥር 4 · Verse 4
ከአካል ሰው እንዳልሮጥ ዘመን ገፋ ብዬ
ማስተዋልህ ጐሎት የሥጋ አእምሮዬ
በለቅሶ ሸለቆ በወሰንከው ቦታ
ፈቃድህን እንዳውቅ እምነቴን አበርታ
አዝማች · Chorus
በክብር ፀባዖቱ ገናናው ዙፋን ሥር ካለው
ፅዋዬም በፊትህ ሞልቶ ተርፎ ሳየው
እንባዬን አፈሳለሁ በምሥጋናም በለቅሶም
አምላኬ በቃህ እስኪለኝ ዓይኖቼን አብሶ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ