ክብሩ ይስፋ
Kebru Yesfa
1987 · ትራክ 6 · 2:22 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
የማልወጣው ይመስለኝና
እምነቴ ፍፁም ይከዳኝና
ደንግጬ ሳለሁ በሥጋት ስፈርስ
አይዞህ ይለኛል ኢየሱስ
አዝማች · Chorus
ክብሩ ይስፋ ለመድኃኒዓለም (፬x)
ቁጥር 2 · Verse 2
የታል እግዚአብሔር ብዬ ስናገር
ማየት ሲሳነኝ ዓይኔ ሲታወር
ብርሃን ሆኖ ሁሉን ሊያሳየኝ
ኢየሱስ ብቅ ሲል ይኸው ታየኝ
አዝማች · Chorus
ክብሩ ይስፋ ለመድኃኒዓለም (፬x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ያለፈው ውለታ ትጋቱ ሁሉ
ቢዘነጋልኝ ያ ብርታት ኃይሉ
መፍገምገም ይዞት ጠላቴ ሲያዝ
ኢየሱስ ብቅ አለ እኔን ሊያግዝ
አዝማች · Chorus
ክብሩ ይስፋ ለመድኃኒዓለም (፬x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ፍቅሩ የሚጣፍጥ ልዩ ነውና
ትዕግሥቱም ፍፁም አያልቅምና
አቻ የሚሆነው የለውምና
ለኢየሱስ ይሁን ምሥጋና
አዝማች · Chorus
ክብሩ ይስፋ ለመድኃኒዓለም (፬x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ