የምሥራቹ ቃል
Yemeserachu Qal
1987 · ትራክ 10 · 3:17 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ጌታህን አመስግን ክርስቲያን ተነሣ
ልብህን ከእጆችህ ጋር ወደ አምላክህ አንሣ
ኢየሱስ ተወልዷል የምሥራች ተናገር
እግዚአብሔር አምላክህን አመስግን በመዝሙር
አዝማች · Chorus
የምሥራቹ ቃል በምድር ተሰማ
በከብቶች በረት ውስጥ በቤተልሔም ከተማ
ምንም ጊዜው ቢረዝም ቢታይም እርቆ
ኢየሱስ ተወለደ ዘመኑን ጠብቆ
ቁጥር 2 · Verse 2
የአዋጅ ነጋሪ ድምፅ በምድር ሲያስተጋባ
የነቢያት ትንቢት ፍፁም ሳይዛባ
ኢየሱስ ተወለደ መዳን ለሰው ሆኗል
ዕልል በል ! ተናገር የምሥራቹን ቃል
አዝማች · Chorus
የምሥራቹ ቃል በምድር ተሰማ
በከብቶች በረት ውስጥ በቤተልሔም ከተማ
ምንም ጊዜው ቢረዝም ቢታይም እርቆ
ኢየሱስ ተወለደ ዘመኑን ጠብቆ
ቁጥር 3 · Verse 3
የቀደመው አዳም ቢሞት በኃጥያቱ
አምላክ አልተወንም አልቆበት ምሕረቱ
አማኑኤል ተወልዷል ምድር ታስተጋባ
አመስግን በአፍህ በእጆችህ ጭብጨባ
አዝማች · Chorus
የምሥራቹ ቃል በምድር ተሰማ
በከብቶች በረት ውስጥ በቤተልሔም ከተማ
ምንም ጊዜው ቢረዝም ቢታይም እርቆ
ኢየሱስ ተወለደ ዘመኑን ጠብቆ
ቁጥር 4 · Verse 4
የጠላትን ምሽግ በሥልጣን ሰባሪ
የንጋት ኮከብ ነው ስሙን አስከባሪ
እመን ትድናለህ ኢየሱስ ተወልዷል
ከዚያም አልፎ ተርፎ በበደልህ ሞቷል
አዝማች · Chorus
የምሥራቹ ቃል በምድር ተሰማ
በከብቶች በረት ውስጥ በቤተልሔም ከተማ
ምንም ጊዜው ቢረዝም ቢታይም እርቆ
ኢየሱስ ተወለደ ዘመኑን ጠብቆ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ