Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

አልተማረም አሉኝ

Altemarem Alugn

ትራክ 4 · 5:47 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

የማመልከው አምላክ ሳይንስ አይጨብጠው

የእብድ ቃላት ብዛት በእውነት አይገምተው

መስፈሳዊ አይኖች ተከፍተው ካላዩት

ቃሉ ሞኝነት ነው አውቀናል ለሚሉት

ሞኝ ነው አልተማረም አሉኝ

ለእግዚአብሔር አድሬለት ቢያዩኝ

ትርፌን እና ጥቅሜን ባለማወቃቸው

እኔ አዘንኩላቸው (፪x)

ይልቅስ ሳይጨልም መዝጊያው ሳይቆለፍ

የሰው ልጅ ይመለስ

ለሚጠፋው አለም ጉልበቱን ከማፍሰስ (፪x)

የሚጠፋ ጥሪት ማከማቸት ትቼ

ዘላለማዊውን ለማግኘት ዘይጄ

ጌታዬን የሙጥኝ ብዬ መወሰኔ

ከአዋቂዎች በላይ አልሆንኩም ወይ እኔ

ሞኝ ነው አልተማረም አሉኝ

ለእግዚአብሔር አድሬለት ቢያዩኝ

ትርፌን እና ጥቅሜን ባለማወቃቸው

እኔ አዘንኩላቸው (፪x)

ይልቅስ ሳይጨልም መዝጊያው ሳይቆለፍ

የሰው ልጅ ይመለስ

ለሚጠፋው አለም ጉልበቱን ከማፍሰስ (፪x)

ምድር እና ሰማይን ያበጀው ፈጣሪ

አይመረመርም ገብቶ ልብራቶሪ

ቁጥርን ከቁጥር ጋር ሲያጋጩ ቢኖሩ

አያዩትም ጌታን እሩቅ ነው ሃገሩ

ሞኝ ነው አልተማረም አሉኝ

ለእግዚአብሔር አድሬለት ቢያዩኝ

ትርፌን እና ጥቅሜን ባለማወቃቸው

እኔ አዘንኩላቸው (፪x)

ይልቅስ ሳይጨልም መዝጊያው ሳይቆለፍ

የሰው ልጅ ይመለስ

ለሚጠፋው አለም ጉልበቱን ከማፍሰስ (፪x)

ሰአቱ ገና አለ ጊዜአችን አልከፋም

እግዚአብሔር ደጁን በሰው ልጅ አልዘጋም

ከማንቀላፋቱ ነቅቶ ለታረመ

ብርሃን ነው ገና ዛሬ መች ጨለመ

ሞኝ ነው አልተማረም አሉኝ

ለእግዚአብሔር አድሬለት ቢያዩኝ

ትርፌን እና ጥቅሜን ባለማወቃቸው

እኔ አዘንኩላቸው (፪x)

ይልቅስ ሳይጨልም መዝጊያው ሳይቆለፍ

የሰው ልጅ ይመለስ

ለሚጠፋው አለም ጉልበቱን ከማፍሰስ (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ