ያምላኬ ቃል አያረጅም
Yamlakie Qal Ayarejem
ትራክ 1 · 3:04 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ያምላኬ ቃል አያረጅም
የኢየሱስ ቃል አያረጅም
ዘለዓለም ይኖራል እያበራ
ከሚያምኑት ጋራ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ተስፋ ስቆርጥ ያጽናናኛል
አቅፎ ደግፎ ያኖረኛል
በደሙ አጥቦ አንጽቶኛል
ኮብልዬ እንዳልሄድ ይጠብቀናል
አዝማች · Chorus
ያምላኬ ቃል አያረጅም
የኢየሱስ ቃል አያረጅም
ዘለዓለም ይኖራል እያበራ
ከሚያምኑት ጋራ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በዓለም ጉዞዬ ይደግፈኛል
ፍፁም ላይተወኝ ተስፋ ሰጥቶኛል
አልተወውም አይተወኝም
የኢየሱሴ ነኝ እስከዘለዓለም
አዝማች · Chorus
ያምላኬ ቃል አያረጅም
የኢየሱስ ቃል አያረጅም
ዘለዓለም ይኖራል እያበራ
ከሚያምኑት ጋራ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ሥጋዬ ደክሞ ነፍሴ ተጨንቃ ስታንቀላፋ
የአምላኬ ቃል ያነቃኛል በሰጠኝ ተስፋ
ልጁ ሆኛለሁ ዳግም ወልዶኛል
ኃጢአቴን ሁሉ ደምስሶልኛል
ጌታዬ አቅፎኝ በእርሱ ስር ካለሁ
ብርሃን እያየሁ እጓዛለሁ
አዝማች · Chorus
ያምላኬ ቃል አያረጅም
የኢየሱስ ቃል አያረጅም
ዘለዓለም ይኖራል እያበራ
ከሚያምኑት ጋራ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ከሚያምኑት ጋራ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ