ክብር ይገባሃል
Keber Yegebahal
ትራክ 15 · 2:31 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
እግዚአብሔር ነገሠ ክብር ለበሰ
ታጠቀ ኃይልንም ለበሰ
ዓለምን አጸናት አቆማት
ምሕረቱም ድንቅ ዘለዓለማዊ
አዝማች · Chorus
ክብር ይገባሃል የእኛ አምላክ (፪x)
ዙፋንም ምሥጋናም ለአንተ ነው (፪x)
ክብር ሃሌሉያ (፫x) ክብር ሃሌሉያ
ቁጥር 2 · Verse 2
ዘለዓለማዊ አምላክ አንተ ነህ
ዝግጁ ነው ከጥንት ዙፋንህ
ወንዞች ከፍ አደረጉ ድምጻቸውን
ተራሮች ጨሱ ሰጡህ ክብርን
አዝማች · Chorus
ክብር ይገባሃል የእኛ አምላክ (፪x)
ዙፋንም ምሥጋናም ለአንተ ነው (፪x)
ክብር ሃሌሉያ (፫x) ክብር ሃሌሉያ
ቁጥር 3 · Verse 3
ከብዙ ውሃዎች ድምጽ ይልቅ
ከታላቅ ሞገድም ድምጽ ይልቅ
ጌታችን አንተ ነህ ኃያል ድንቅ
ምስክር ታማኝ አንተ ታላቅ
አዝማች · Chorus
ክብር ይገባሃል የእኛ አምላክ (፪x)
ዙፋንም ምሥጋናም ለአንተ ነው (፪x)
ክብር ሃሌሉያ (፫x) ክብር ሃሌሉያ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ