የነፍሴ ንጉሥ
Yenefsie Negus
ትራክ 2 · 3:01 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
የነፍሴ ንጉሥ ኢየሱስ
የሕይወቴ ንጉሥ ኢየሱስ
በሰማይ በምድር ቅዱስ ቅዱስ
የነፍሴ ንጉሥ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
በድንግዝግዝ ብርሃን በምኞት ሸለቆ
ቆሜ ሳነባ አየኝ ሕይወቴ ተነክቶ
የዘረጋው እጁ አልደርስለት ብሎ
አወጣኝ አምላኬ ለእኔ ተንጠልጥሎ
አዝማች · Chorus
የነፍሴ ንጉሥ ኢየሱስ
የሕይወቴ ንጉሥ ኢየሱስ
በሰማይ በምድር ቅዱስ ቅዱስ
የነፍሴ ንጉሥ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
እጆቹ ቆሰሉ ግንባሩ ተበሳ
ለእኔ ለሙት ሕይወት እንዲኖረኝ ተስፋ
ጐኑን ለጦር ሰጥቶ ደሙን አጐረፈ
የእኔን አፈር ገላ ከሞት አተረፈ
አዝማች · Chorus
የነፍሴ ንጉሥ ኢየሱስ
የሕይወቴ ንጉሥ ኢየሱስ
በሰማይ በምድር ቅዱስ ቅዱስ
የነፍሴ ንጉሥ (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ጀርባውን ለጅራፍ አጋልጦ ሰጠና
ተዘነጋ በእርሱ የእኔ ጉስቁልና
እርቃኑን ተጋልጦ ሆኖ ጐስቋላ ሰው
ሚስጢሬን ደብቋል ሕይወቴ እንዴት ትርሳው?
አዝማች · Chorus
የነፍሴ ንጉሥ ኢየሱስ
የሕይወቴ ንጉሥ ኢየሱስ
በሰማይ በምድር ቅዱስ ቅዱስ
የነፍሴ ንጉሥ (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
የድካሙ ብዛት ለእኔ ፋታ ሆነኝ
የቀራንዮ ደም ከኃጢአት አዳነኝ
ጽድቁን ተመርኩዤ ስራዬን ደብቄ
ተጓዝኩኝ ከእርሱ ጋር ድካሜን አውቄ
አዝማች · Chorus
የነፍሴ ንጉሥ ኢየሱስ
የሕይወቴ ንጉሥ ኢየሱስ
በሰማይ በምድር ቅዱስ ቅዱስ
የነፍሴ ንጉሥ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ