ጌታ ረዳቴ ነው
Gieta Redatie New
ትራክ 9 · 2:21 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ጌታ ረዳቴ ነው በድካሜ
መስቀሉን ይዣለሁ ተሸክሜ
ልለየው ብሞክር ልክደው
ፍቅሩ ግድ ይለኛል እንዳልተወው
ቁጥር 1 · Verse 1
ሕይወቴ ሲደክም ሲዝልብኝ
ረዳት የሌለኝ እኔን ሲመስለኝ
ጌታ በክንዶቹ ያነሳኛል
ደረቁን ሕይወቴን ያረካዋል
አዝማች · Chorus
ጌታ ረዳቴ ነው በድካሜ
መስቀሉን ይዣለሁ ተሸክሜ
ልለየው ብሞክር ልክደው
ፍቅሩ ግድ ይለኛል እንዳልተወው
ቁጥር 2 · Verse 2
አንዴ በሸለቆ እንዲያ ሳለቅስ
አንዴ በተራራ ስፈነጥዝ
የመስቀሉን መንገድ ስለማመድ
ብዙ ትምህርት አለው ልማር : ብወድ
አዝማች · Chorus
ጌታ ረዳቴ ነው በድካሜ
መስቀሉን ይዣለሁ ተሸክሜ
ልለየው ብሞክር ልክደው
ፍቅሩ ግድ ይለኛል እንዳልተወው
ቁጥር 3 · Verse 3
እኔ ተስፋ አልቆርጥም እቆማለሁ
የሕይወቴን መንገድ መርጫለሁ
እደክማለሁ እንጂ ከቶ አልፈራም
የሕይወትን እራስ አልክደውም
አዝማች · Chorus
ጌታ ረዳቴ ነው በድካሜ
መስቀሉን ይዣለሁ ተሸክሜ
ልለየው ብሞክር ልክደው
ፍቅሩ ግድ ይለኛል እንዳልተወው (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ