ካልባረከኝ
Kalbarekegn
ትራክ 13 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
ለብቻዬ ልኖር ፈቃድህ ከሆነ
ሌላው አይገደኝም ሕይወቴ ከዳኔ
ሲሆን እስከንጋት ልታገልህና
ስደደኝ ጌታ ሆይ ሕይወቴን ባርክና
አዝማች · Chorus
ካልባረከኝ አለቅህም (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
ካልባረከኝ አለቅህም (፪x)
ከመምበርከክ ብዛት በጸሎት ትግል
ፈቃድህ ከሆነ ጉልበቴ ይዛል
እያነከስኩ ይሁን እከተልሃለሁ
እጅህን ዘርጋብኝ በረከት እሻለሁ
አዝማች · Chorus
ካልባረከኝ አለቅህም (፪x)
ቁጥር 3 · Verse 3
ሊነጋ ሲጀምር ሰማዩም ሲቀላ
ወደዚህ እሄዳለሁ ነፍሴ እንዲህ ዝላ
ሕይወቴን ብቻ ባርክ ሌላ አልመኝም
ሥም እንደው ቀሪ ነው ሥም አያድነኝም
አዝማች · Chorus
ካልባረከኝ አለቅህም (፪x)
ቁጥር 4 · Verse 4
ካልባረከኝ አለቅህም (፪x)
እንደ ያዕቆብ ዛሬ ጩኸቴን ስማና
ስደደኝ ጌታ ሆይ ሕይወቴን ባርክና
ፈቃድህ ከሆነ ስሜንም ለውጠው
ሰው እንዳለው ሳይሆን አንተ እንደ ወደድከው
አዝማች · Chorus
ካልባረከኝ አለቅህም (፪x)
ቁጥር 5 · Verse 5
ካልባረከኝ አለቅህም (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ