Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

ድል በድል ጐዳና

Del Bedel Godana

ትራክ 7 · 2:36 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

ድል በድል ጐዳና (፪x)

ክርስቲያን አሸነፈ ኢየሱስ አለውና (፪x)

ያን ድቅድቅ ጨለማ የሞትን ሸለቆ

ታገለው ክርስቲያን የእምነት ትጥቁን ታጥቆ

አሻፈረኝ ብሎ ለእርሱ ላይረታ

በድል ጥሎት ወጣ በጌታው መከታ

ድል በድል ጎዳና ድል በድል ጎዳና

ክርስቲያን አሸነፈ ኢየሱስ አለውና (፪x)

የጥሻው ጨለማ ብርሃን ወጣበት

ክርስቲያን በእምነት ሰይፍ አንዴ ቢዘምትበት

የማጥመጃው ሜዳ በደም አጥለቅልቆ

ሕያው ዘር ዘራበት እንዲበቅል አውቆ

ድል በድል ጎዳና ድል በድል ጎዳና

ክርስቲያን አሸነፈ ኢየሱስ አለውና (፪x)

ጋሻ ጦሩ መንፈስ ፍላጻው እምነቱ

ማን ሊቋቋመው ነው ያን ክንደ ብርቱ

ሊያጠምዱት ሊያስቀሩት አጥብቀው ቢጥሩ

ከአምላኩ ደም ቅጥር አልነቀለም እግሩን

ድል በድል ጎዳና ድል በድል ጎዳና

ክርስቲያን አሸነፈ ኢየሱስ አለውና (፪x)

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ