ወንዙ ከፊት ሲታይህ
Wenzu Kefit Sitayeh
ትራክ 6 · 2:04 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ወንዙ ከፊት ሲታይህ
ቢመስልህ የሚውጥህ
ታምነህ ጉዞህን ቀጥል
ጌታ ይመራሃል
ቁጥር 1 · Verse 1
የማዕበሉ ጌታ ቀድሞሃል
ተከተለኝ አይዞህ ይልሃል
ቀና ነው መንገዱ ተጽናና
የናዝሬቱ ኢየሱስ አለና
አዝማች · Chorus
ወንዙ ከፊት ሲታይህ
ቢመስልህ የሚውጥህ
ታምነህ ጉዞህን ቀጥል
ጌታ ይመራሃል
ቁጥር 2 · Verse 2
ባሕሩ አፍ ለአፍ ሞልቶ
ወጀብ ሲያናውጠው በርትቶ
ሰንጥቀህ ማለፍን ብትፈራ
ቶሎ ብለህ ጌታህን ጥራ
አዝማች · Chorus
ወንዙ ከፊት ሲታይህ
ቢመስልህ የሚውጥህ
ታምነህ ጉዞህን ቀጥል
ጌታ ይመራሃል
ቁጥር 3 · Verse 3
ሁሉንም በቃሉ ያዘዋል
ፍጥረትም ለእርሱ ይታዘዛል
ሁሉን ቻይ ጌታ አለ ከፊትህ
ጠላት ሲረፈረፍ ታያለህ
አዝማች · Chorus
ወንዙ ከፊት ሲታይህ
ቢመስልህ የሚውጥህ
ታምነህ ጉዞህን ቀጥል
ጌታ ይመራሃል
ቁጥር 4 · Verse 4
በባሕሩ ጉዞ ብትዝልም
አይዞህ መንገድ ላይ አትቀርም
ጌታህ አጠገብህ አለና
እርዳኝ በለው ጠጋ በልና
አዝማች · Chorus
ወንዙ ከፊት ሲታይህ
ቢመስልህ የሚውጥህ
ታምነህ ጉዞህን ቀጥል
ጌታ ይመራሃል (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ