Lyriqaሊሪቃ · የመዝሙር ግጥሞች

እንዴት ድንቅ አምላክ ነው

Endiet Dinq Amlak New

ትራክ 11 · 2:27 · አማርኛ

▣ አቅርብ / Present✎ እርማት ጠቁም

የደን ልማቱ የገደል ስርገቱ

የወንዝ እርዝመቱ የቀላይ ውበቱ

የቆንጆ ገጽታው የቦታ ከፍታው

የባሕር ጥልቀቱ የሜዳ ስፋቱ

እኛ ምናመልከው መሠረቱ

እንዴት ድንቅ አምላክ ነው እኛ ምናመልከው

እንደምን ኃያል ነው እኛ ምንሰግድለት

የኃይል ሁሉ ጉልበት የፍጥረት መሠረት

የሽቶ መዓዛው የሙዚቃ ቃናው

የለምለም እርካታው የመዝናኛ ቦታው

የመፋቅር ወዙ የትዳር ማገዙ

የፍጥረት ድምቀቱ የሰማይ ርቀቱ

እኛ ምናመልከው መሠረቱ

እንዴት ድንቅ አምላክ ነው እኛ ምናመልከው

እንደምን ኃያል ነው እኛ ምንሰግድለት

የኃይል ሁሉ ጉልበት የፍጥረት መሠረት

የአበቦች ፍካታ የወፎች ጫጫታ

የቀለም መዋሃድ የሰው ልጅ መዋደድ

የእምነት እርካታ ሰላምና ደስታ

የፅዮን ውበቱ የእውነት ጥራቱ

እኛ ምናመልከው መሠረቱ

እንዴት ድንቅ አምላክ ነው እኛ ምናመልከው

እንደምን ኃያል ነው እኛ ምንሰግድለት

የኃይል ሁሉ ጉልበት የፍጥረት መሠረት

ጐህ ሲቀድ ማለዳ ጨለማ ሲከዳ

የፀሐዩ ሙቀት የከዋክብት ብዛት

የደመናት ክምር ንጹህ ተስማሚ አየር

ሁሉን በስርዓቱ መሪ ለፍጥረቱ

እኛ ምናመልከው መሠረቱ

እንዴት ድንቅ አምላክ ነው እኛ ምናመልከው

እንደምን ኃያል ነው እኛ ምንሰግድለት

የኃይል ሁሉ ጉልበት የፍጥረት መሠረት

ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ