ተራመድ
Teramed
ትራክ 20 · 2:08 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ተራመድ በርታ በርታ
ጉዞህንም ፈጽም
ቁጥር 1 · Verse 1
ሕይወትንም አድን
የመከራ ጉም በላይ ቢያንዣብብ
አለና ኢየሱስ ፍፁም አታስብ
ቢመስልህ ጉዞ ፍፁም ተራራ
ደጋፊ አለህ ፍፁም አትፍራ
አዝማች · Chorus
ተራመድ በርታ በርታ
ጉዞህንም ፈጽም
ቁጥር 2 · Verse 2
ሕይወትህንም አድን
በኃጢአት ቁስል ብትማቅቅም
በሱ ከታመንክ ፍፁም አትወድቅም
ስለሚመለስ ጌታ ከሰማይ
መብራትህ ይብራ ለዓለምም ይታይ
አዝማች · Chorus
ተራመድ በርታ በርታ
ጉዞህንም ፈጽም
ቁጥር 3 · Verse 3
ሕይወትህንም አድን
አትሞኝ ከቶ በዓለም ደስታ
ስለማታገኝ የሕይወት እርካታ
መቅረዝህ ይብራ ቁም ተዘጋጅተህ
ጌታ ሲመለስ ትነጠቃለህ
አዝማች · Chorus
ተራመድ በርታ በርታ
ጉዞህንም ፈጽም
ቁጥር 4 · Verse 4
ሕይወትህንም አድን
ቋሚ ጓደኛ ስላለህ ኢየሱስ
በእምነት ተጋደል በተስፋ ገስግስ
ዓለምን አትይ ማብለጭለጯንም
ተስፋ ከመቁረጥ አታድንህም
አዝማች · Chorus
ተራመድ በርታ በርታ
ጉዞህንም ፈጽም
ቁጥር 5 · Verse 5
ሕይወትህንም አድን (፪x)
ሕይወትህንም አድን
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ