ጠፊዋን ዓለም
Tefiwan Alem
ትራክ 19 · 2:55 · አማርኛ
አዝማች · Chorus
ጠፊዋን ዓለም ተለይቼ
ለዘለዓለም ተሰናብቼ
የሚሞተው ተለውጦ
የማይሞተውን ኢየሱስን ለብሶ (፪x)
ቁጥር 1 · Verse 1
ከጌታ ጋር ልኖር እናፍቃለሁ
ዓለምንና ሃሳቧን ትቻለሁ
ከላይ የሚመጣውን እጠብቃለሁ
በቅጽበት ወደእርሱ እነጠቃለሁ
አዝማች · Chorus
ጠፊዋን ዓለም ተለይቼ
ለዘለዓለም ተሰናብቼ
የሚሞተው ተለውጦ
የማይሞተውን ኢየሱስን ለብሶ (፪x)
ቁጥር 2 · Verse 2
በጉጉት ናፍቆት ፊቱን ሳይ
ኢየሱስን ሳገኝ በላይ በሰማይ
ፊቱን ስመለከት እምባዬን ሲያይ
እየዳሰሰ ዓይኔን ያብሳል
አዝማች · Chorus
ጠፊዋን ዓለም ተለይቼ
ለዘለዓለም ተሰናብቼ
የሚሞተው ተለውጦ
የማይሞተውን ኢየሱስን ለብሶ
ቁጥር 3 · Verse 3
ጌታ መምጣቱ ያሳውጃል
በደጅ እንደቆመ ሕይወቴም ያውቃል
ቀኑ እንደደረሰ ተረድጄ
ተጨማሪ ዘይት ልግዛ ተግቼ
አዝማች · Chorus
ጠፊዋን ዓለም ተለይቼ
ለዘለዓለም ተሰናብቼ
የሚሞተው ተለውጦ
የማይሞተውን ኢየሱስን ለብሶ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ