ከባሕር ሞገድ
Kebaher Modeg
ትራክ 14 · 2:03 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
አክሊሌን በደምህ ልሸሽገው
የሰው ልጅ ጠላት ሰይጣን እንዳይሰርቀው
መፈታተኑን አላቋረጠም
አንተ እስክትመጣ በክብር ወደዚች ዓለም
አዝማች · Chorus
ከባሕር ሞገድ ከአየር ነጐድጓድ
በሚበልጥ ኃይልህ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ወልድ
አጥበኸኝ እኔን ድኛለሁ ጌታ
ቁጥር 2 · Verse 2
ለአክሊልህ ያብቃኝ ኢየሱስ እንዳልረታ
ቁጥር 3 · Verse 3
ጠበቃዬና አክሊሌን ይዘህ
በመርከብህ ውስጥ ልግባ እኔም እንደ ኖህ
ጐልማሳነቴን ሩጫዬን በቃኝ
አክሊሌን ከአንተ ኢየሱስ ለመውሰድ አብቃኝ
አዝማች · Chorus
ከባሕር ሞገድ ከአየር ነጐድጓድ
በሚበልጥ ኃይልህ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ ወልድ
አጥበኸኝ እኔን ድኛለሁ ጌታ
ቁጥር 4 · Verse 4
ላክሊልህ ያብቃኝ ኢየሱስ እንዳልረታ
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ