አቤት እንዴት ታላቅ ነህ
Abiet Endiet Talaq Neh
ትራክ 1 · አማርኛ
ቁጥር 1 · Verse 1
በቃ አልፈልግም ልቤን ውሰደው
አዕምሮዬን ግዛው ላአንተው አድርገው
ዝም ልበልና ኃይልህን ልመልከት
ሌላው ሃሣቤ ይብቃ ይከተት
አዝማች · Chorus
አቤት እንዴት ታላቅ ነህ?
እንዴት ታማኝ ነህ?
እንዴት ፍፁም ነህ?
የዘለዓለም አምላክ የማትለወጥ
ቁጥር 2 · Verse 2
የፍቅር አምላክ ጸንተህ ትኖራለህ
ሌት በመኝታ እንዳስብህ አንተን
ቀን በሥራዬ እንዳውጠነጥን
ነህና ለነፍሴ ዕርካታና ደስታ
ክብርህን ላስበው ሁሌ ጠዋት ማታ
አዝማች · Chorus
አቤት እንዴት ታላቅ ነህ?
እንዴት ታማኝ ነህ?
እንዴት ፍፁም ነህ?
የዘለዓለም አምላክ የማትለወጥ
ቁጥር 3 · Verse 3
የፍቅር አባት ጸንተህ ትኖራለህ
እጄን በአፌ ላይ አድርጌ ተደነቅሁ
ሥራህንም ሳየው በደስታ ተሞላሁ
በዕውነት ተረዳሁ የአንተን ታላቅነት
እንዲሁም አስተዋልሁ የእኔን ውዳቂነት
አዝማች · Chorus
አቤት እንዴት ታላቅ ነህ?
እንዴት ታማኝ ነህ?
እንዴት ፍፁም ነህ?
የዘለዓለም አምላክ የማትለወጥ
ቁጥር 4 · Verse 4
የፍቅር አባት ጸንተህ ትኖራለህ
ለአንተ ሚገባህ ክብርን ለመስጠት
በመንፈስ ሳስብህ ያኔ ተረዳሁት
አሁን ቃል ኪዳኔ የመጨረሻው
ተዋርጄ እንድኖር ነው ለአንተ ምሻው
አዝማች · Chorus
አቤት እንዴት ታላቅ ነህ?
እንዴት ታማኝ ነህ?
እንዴት ፍፁም ነህ?
የዘለዓለም አምላክ የማትለወጥ
ቁጥር 5 · Verse 5
የፍቅር አባት ጸንተህ ትኖራለህ (፪x)
ምንጭ፦ ግጥሙ በ WikiMezmur ማኅበረሰብ የተገለበጠ ነው። የግጥሙ መብት የደራሲው ነው — የመብት ጥያቄ